ቤት ለ እንቦሳ!
ህዳር 10 ፤ 2015 ከ የረር ተራሮች ስር በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዜና ተበስሯል፡፡ 310 ሆሴዕ ሪልስቴትን አምነው ፤ቁልፎቻቸውን በተስፋ ሲጠባበቁ የነበሩ ደንበኞች በ 23,000 ካሬ.ሜ ላይ በተንጣለለው መንደራቸው እንቦሳ አስረዋል! የጠዋቷን ጮራ ተከትሎ የተጀመረው ደማቅ የቁልፍ ርክክብ ስነ-ስርዓት የከተማይቱ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በድምቀት የተከፈተ ሲሆን ፤ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የቤት ባለንብረቶች እንዲሁም ልዩ ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውበታል፡፡
በከንቲባዋ ከተመራው ምርቃት እና ጉብኝት በኋላም የችግኝ መትከል መርሀ-ግብር ተፈፅሟል፡፡ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግርም “በመዲናችን የሚታየውን ስር-ሰደድ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ለመቅረፍ ልክ እንደ ሆሴዕ ሪልስቴት ያሉ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ለነዋሪዎች የረር ሆምስን የመሰሉ ሰፊ እና ይህንን ችግር ማቃለል በሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይ በትጋት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
” በመድረኩም የሆሴዕ ሪልእስቴት ባለቤት አቶ የማነ ገ/ስላሴ ፣ ስራ አስፈፃሚው አቶ ሰይፈ ፈቃደን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችም ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመኖሪያ መንደሩ ግንባታ ላይ ጉልህ ሚና የተጫወቱ አካላት የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በስተመጨረሻም ከቤት ባለንብረቶች ጋር የቁልፍ ርክክብ ስነ-ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ፤ የነዋሪዎችን ሁለንተና ጥቅም ለማስጠበቅ ማህበር እንደተቋቋመ ፣ የግል የውሃ እና የመብራት ቆጣሪ እንደተገጠመ እንዲሁም ለሁሉም ነዋሪ የባለቤትነት ካርታ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ሪል እስቴት ታሪክ ባልተለመደ መልኩ ቃል ከገባው ጊዜ 6 ወር በመቅደም ሆሴዕ ሪል እስቴት ለደንበኞቹ 310 ቤቶችን ከተሟላ እና ዘመናዊ መንደር ጋር ገንብቶ በማስረከቡ የተሰማቸውን ከፍተኛ አድናቆት ሁሉም የቤት ባለንብረቶች በደስታ ሲገልፁ እና መኖሪያ ቤቶቻቸውን በመጎብኘት ሲያደንቁ ተስተውለዋል፡፡