We found 0 results. View results
Your search results

ሆሴዕ ሪልስቴት ለመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል ድጋፍ አደረገ።

Posted by hoseadomain on April 25, 2023
0

ሆሴዕ ሪልስቴት የካፒታል ሆቴል እና ሰፖ እህት ኩባንያ ግምታዊ ወጪያቸው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሌሊት ልብሶችና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ሆሴዕ ሪልስቴት ፥ ” በአጭር ጊዜ ውስጥ በሪልስቴት ዘርፍ በመንቀሳቀስ በቅርቡ በአያት 49 አካባቢ በ23 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ለ300 አባወራዎች በ2 ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሪል እስቴት ቤቶችን ገንብቶ በማስረከብ በርካታ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በጥራትና በብቃት ገንብቼ ታሪክ ሰርቻለሁ ” ብሏል።

የሆሴዕ ትሬዲንግ ሀውስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የማነ ገብረሥላሴ ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር የአንድ ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የጽዳት መገልገያ ቁሳቁሶችን በእርዳታ ለግሰዋል።

ሆሴዕ ሪልስቴት ከሚያከናውኗቸው ስኬታማ ሥራዎች ባሻገር በመቄዶንያ አረጋውያንና ህሙማን ማዕከል በመገኘት ትናንት በሙያና በጉልበታቸው ሀገር ላቆሙ አረጋውያንና ልዩ ልዩ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚሆን አንሶላ፣ ፎጣ፣ ብርድልብስ፣ ፍራሾችን እና የተለያዩ የጽዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በብር 1 ማሊዮን በመግዛት ለመቄዶንያ አረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል መሥራች ለዶ/ር ቢኒያም በለጠ በሆሴዕ ሪልስቴት ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ ልዑል አማካኝነት ተበርክቷል፡፡

የሆሴዕ ትሬዲንግ ሀውስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ኩባንያው እስከዛሬ የተለያዩ ሀገራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን በቀጣይም እንደ መቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ላሉ በጎ ተግባር ላይ ለሚሳተፉ ተቋማት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥለል ብሏል።

Compare Listings